በዘንድሮው መኸር ወቅት የጥራጥሬ ሰብሎች ምርት አምና ከተገኘው ምርት ጋር ሲወዳደር 1.64 በመቶ ጭማሪ ያሳየ ሲሆን በተመሳሳይም ዘንድሮ የተገኘው የቅባት ሰብሎች ምርት አምና ከተገኘው ምርት ጋር ሲወዳደር የ6.93 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

በሶስቱ የመኸር ድህረ-ሰብል ምርት ወቅቶች (ማለትም 2007፣ 2008 እና 2009) ያለው የሰብል ምርታማነት ሁኔታ ሲታይ በ2009 የመኸር ወቅት ድህረ-ሰብል ምርት በብርዕና አገዳ ሰብሎች በ2007 ከተመዘገበው ጋር ሲወዳደር በ2009 የተገኘው የሩዝ ምርታማነት መጠነኛ ቅናሽ ከማሣየቱ በስተቀር በሌሎቹ በሁሉም የብርዕና የአገዳ ሰብል ዓይነቶች በ2009 የተገኘው የሰብል ምርታማነት ከፍተኛ ጭማሪ ታይቶበታል፡፡

ጥራጥሬ ሰብሎችን በሚመለከት በ2009 ዓ.ም. የተገኘው የነጭ አደንጓሬ ምርታማነት በ2007 ከተመዘገበው ጋር ሲወዳደር መጠነኛ ቅናሽ ያሣየ ሲሆን በሌሎቹ የጥራጥሬ የሰብል ዓይነቶች ግን በ2009 የተገኘዉ ምርታማነት ጭማሪ አሣይቷል፡፡ በተመሳሳይ በ2009 የተገኘው የቅባት ሰብሎች ምርታማነት ከጎመንዘር በስተቀር በሌሎቹ የቅባት እህሎች ላይ ጭማሪ ተይቷል፡፡

የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ በየዓመቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ የግብርና ስታቲስቲክስ ናሙና ጥናት በማካሄድ ለበርካታ ዓመታት የተለያዩ የግብር ና መረጃዎችን ለተጠቃሚዎች በማቅረብ ላይ ይገኛል፡፡ cont...

  • Inflation Rate for the Month of April 2019 is 12.9%
  • National Poverty head count indices  in 2010/2011 29.6%
  • Rural Poverty head count indices  in 2010/2011 30.4%
  • Urban Poverty head count indices  in 2010/2011 25.7%
  • National Poverty head count indices  in 2015/2016 23.5%
  • Rural Poverty head count indices  in 2015/2016 25.6%
  • Urban Poverty head count indices  in 2015/2016 14.8%
  • National income inequality using GINI Coefficient in 2010/11 is 0.298
  • Rural income inequality using GINI Coefficient in 2010/11 is 0.27
  • Urban income inequality using GINI Coefficient in 2010/11 is 0.37
  • National income inequality using GINI Coefficient in 2015/16 is 0.328
  • Rural income inequality using GINI Coefficient in 2015/16 is 0.28
  • Urban income inequality using GINI Coefficient in 2015/16 is 0.38
  • GDP per Capital (in US Dollar) in 1999/00 is 129
  • GDP per Capital (in US Dollar) in 2007/08 is 262
  • GDP per Capital (in US Dollar) in 2015/16 is 794
  • Source:-  Ethiopia's Progress Towards Eradicating Poverty: An  Interim Report on 2015/16
  • Poverty Analysis Study, National Planning Commission, September 2017

 

 

Copyright © Central Statistical Agency - Ethiopia, 2010 / 2018