በአገራችን ለአራተኛ ጊዜ የሚካሔደው የሕዝብና ቤት ቆጠራ ከየካቲት 4-14 ቀን 2010 ዓ.ም እንደሚካሔድ የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢራቱ ይገዙ ጥቅምት 7 ቀን 2010 ዓ.ም በጽ/ቤታቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቁ፡፡

የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ከተለያዩ የመንግሥት የሚዲያ ተቋማት ለተጋበዙ ጋዜጠኞች ለአራተኛው ዙር አገር አቀፍ የሕዝብና ቤት ቆጠራ የሚካሔደውን ዝግጅት አስመልክቶ ባዘጋጀው በዚህ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ዋና ዳይሬክተሩ እንደገለጹት ቀደም ሲል በሕዳር ወር 2009 ዓ.ም እንዲካሔድ ታቅዶ የነበረው የሕዝብና ቤት ቆጠራ በተለያዩ ምክንያቶች ወደየካቲት ወር 2010 ዓ.ም ተዛውሯል፡፡

ከምክንያቶቹ መካከልም ከቆጠራው በፊት እስከ ሰኔ 30 ቀን 2009 ዓ.ም እንዲጠናቀቅ ዕቅድ ተይዞለት የነበረው የቆጠራ ቦታ ካርታ ዝግጅት በተለይ በሶማሌ ክልላዊ መንግሥት ስር ባሉ አንዳንድ አካባቢዎች በተከሰተው ድርቅ ምክንያት የአካባቢው ነዋሪዎች ወደሌላ ቦታ መንቀሳቀሳቸው፣ ለቆጠራው ሥራ አስፈላጊ የሆነው የታብሌት ግዥ ተጨማሪ ጊዜ መጠየቁ እንዲሁም በቆጠራው ወቅት መረጃውን ከታብሌቶች በቀጥታ (online) የሚቀበለውና በዋናው መ/ቤት መደራጀት ያለበት ሰርቨር ውስንነት የነበረው በመሆኑ የተሟላ አቅም እንዲኖረው ለማድረግ ተጨማሪ ጊዜ የጠየቀ በመሆኑ የቆጠራው ቀን እንዲራዘም ለሕዝብ ቆጠራ ኮሚሽን በቀረበ ጥያቄ መሠረት የቆጠራው ጊዜ ከየካቲት 4-14 ቀን 2010 ዓ.ም እንዲካሔድ በኮሚሽኑ የተወሰነ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በተጠቀሰው ጊዜ የሕዝብና ቤት ቆጠራውን በተሳካ ሁኔታ ለማካሔድ በመደረግ ላይ ያሉ ቅድመ-ዝግጅቶችን ሲጠቅሱም በአገሪቱ 150‚000 ያህል የቆጠራ ቦታዎች የተዘጋጁ መሆናቸውን ገልጸው፣ ለእያንዳንዱ የቆጠራ ቦታ አንድ የመስክ ቆጣሪ እንዲሁም ለሁሉም የቆጠራ ቦታዎች 38‚000 የቴክኒክ ተቆጣጣሪዎች የሚያስፈልጉ በመሆኑ በቆጠራው ጊዜ ከ180‚000 በላይ የሰው ኃይል ለማሰማራት ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡ ከዝግጅቶቹ መካከልም ቆጣሪዎች እና ቴክኒክ ተቆጣጣሪዎች የሚሳተፉበት የአሠልጣኞች ሥልጠና እና የሥልጠና ፕሮግራሞችን ማካሔድ ይገኝበታል፡፡

አራተኛውን ዙር የሕዝብና ቤት ቆጠራ ልዩ የሚያደርጉትን ጉዳዮች ሲያስረዱም የቆጠራው መረጃ የሚሰበሰበው በታብሌት ቴክኖሎጂ በዲጂታል ዘዴ መሆኑ እና ከዚህ ቀደም በአማርኛ ቋንቋ ብቻ ይዘጋጅ የነበረው መመሪያ እና የቆጠራ መጠይቅ አሁን ግን በኦሮምኛ፣ በትግርኛ በአፋርኛ እና በሶማሌኛ ቋንቋዎች ጭምር የሚዘጋጅ መሆኑን ጠቅሰው፣ መረጃው ሲሰበሰብ እና ሲጠናቀር ሚስጢራዊነቱን ለመጠበቅና መረጃውን ከመረጃ መንታፊዎች ለመከላከል የሚያስችል ሥርዓት ለማዘጋጀት ከኢንፎርሜሽን መረብ ደሕንነት ኤጀንሲ ጋር በመተባበር አስፈላጊው ቅድመ-ዝግጅት በመደረግ ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይም ለቆጠራው ሥራ አስፈላጊ የሆኑ የትምሕርት እና ቅስቀሳ ሥራዎች ሕትመት የተጀመረ መሆኑን የጠቀሱት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ወደአገር ውስጥ እንደሚገቡ ከሚጠበቁት 180‚000 ያህል ታብሌቶች መካከል 120‚000 ያህል ታብሌቶች በቅርቡ ወደአገር ውስጥ የገቡ በመሆኑ እነዚህን የቆጠራ መሳሪያዎች ለመረከብ እንዲቻል አስፈላጊው የጉምሩክ ሥነሥርዓት እየተከናወነ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡ የታብሌቶቹ ርክክብ እንደተፈጸመም ለቆጠራ ሥራው የሚያስፈልገውን ሶፍትዌር በኤጀንሲው ባለሙያዎች የመጫንና እያንዳንዱን ታብሌት የመፈተሽ ሥራ እንደሚካሔድም ጠቁመዋል፡፡

በቆጠራው ሥራ ላይ በዋናነት በየክልሎቹ የሚገኙ መምህራን፣ የግብርና ኤክስቴንሽን እና የጤና ኤክስቴንሽን ሠራተኞች እንደሚሳተፉ የታወቀ ሲሆን የምልመላ መስፈርቱም የአካል ብቃትን፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ችሎታን እና መልካም ሥነምግባርን ታሳቢ ያደረገ እንደሚሆን ታውቋል፡፡

Contact Us

Ato Biratu Yigezu

General Director

Central Statistical Agency of Ethiopia

Address:- Piassa, Behind Taitu Hotel, Adjacent to Ethio Ceramic Head Office

Telephone:-  011-1-11-7787

                        011-1-11-5131

 • Inflation rate for the month of December 2017 is  13.6
 • Total Population size as of July 1, 2017 94,352, 000
 • Total Male Population size as of July 2017 47,365, 000
 • Total Female Population size as of July 2017 46,987,000
 • Total Population size  urban as of July 1, 2017 19,164, 000
 • Total  Male Population size  urban as of July 1, 2017 9,535, 000
 • Total Female Population size  urban as of July 1, 2017 9,630, 000
 • Total Population size  rural as of July 1, 2017 75,188, 000
 • Total Male Population size rural as of July 1, 2017 37,830, 000
 • Total Female Population size rural as of July 1, 2017 37,357, 000
 • Urban Unemployment 2015 17.5%
 • Literacy rate 2009/10 (or recent) 36% of children under weight (too thin for-age) 2011 29.0%
 • GDP per Capital (in US) 2006/07 255.4
 • National Povertyhead count indices and inequality in 2010/2011 29.6%
 • Rural Povertyhead count indices and inequality in 2010/2011 30.4%
 • Urban Povertyhead count indices and inequality in 2010/2011 25.7%

Copyright © Central Statistical Agency - Ethiopia, 2008 / 2016