በ2009 ዓ.ም መኸር ወቅት ከአነስተኛ የግል ገበሬዎች የተገኘው የምርት መጠን ከአምናዉ የመኸር ወቅት ጋር ሲነጻጸር የምርት መጠኑ የ8.83 በመቶ ወይም የ23.6 ሚሊዮን ኩንታል ጭማሪ አሳይቷል

የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ መላ ሀገሪቱን በመሸፈን ከመስከረም ወር በ2009 ዓ.ም መጀመሪያ እስከ የካቲት ወር መጨረሻ ለአምሰት ወራት ሲያካሄድ የቆየዉን የ2009 ዓ.ም የአነስተኛ ገበሬዎች የ2009 ዓ.ም. የዋናው መኸር ወቅት ድህረ-ሰብል ምርት ናሙና ጥናት ዉጤትን አስመልክቶ ሚያዚያ 19 ቀን 2009 ዓ.ም በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ በ2009 ዓ.ም የመኸር ወቅት ከ290 ሚለዮን ኩንታል በላይ ምርት መገኘቱ ተገለጸ፡፡

ኤጀንሲው የስታቲስቲክስ ጥናቶችና ቆጠራ ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ አማረ ለገሰ በወቅቱ እንደገለጹት በ2009 ዓ.ም በዋናው መኽር ወቅት የሰፋፊና መካከለኛ የንግድ እርሻዎችን፣   የበጋ ወቅት የግል ገበሬዎች የመስኖ እርሻ ድህረ-ሰብል ምርትንና የበልግ ወቅት ሰብል ምርትን ሳያካትት በአነስተኛ የግል ገበሬዎች ብቻ ታርሶ በምግብ ሰብሎች የተሸፈነ መሬት ስፋት 12,574,107.33 ሄክታር ሲሆን በሰብል ዘመኑ የተገኘዉ የምርት መጠን ደግሞ 290,385,593.21 ኩንታል ነው፡፡

ኤጀንሲዉ በሰጠው መግለጫ ከምግብ ሰብሎች ከፍተኛ ጭማሪ (9.75 በመቶ) የታየው በብርዕና አገዳ ሰብሎች ምርት ላይ ነው፡፡ ጤፍ፣ ስንዴ፤ በቆሎ፣ ዳጉሳ፣ ሩዝና ሌሎችም በብርዕና አገዳ ምድብ ስር ያሉ ሰብሎች በሙሉ ጭማሪ አሳይተዋል፡፡ Read More ...

  • Inflation Rate for the Month of April 2019 is 12.9%
  • National Poverty head count indices  in 2010/2011 29.6%
  • Rural Poverty head count indices  in 2010/2011 30.4%
  • Urban Poverty head count indices  in 2010/2011 25.7%
  • National Poverty head count indices  in 2015/2016 23.5%
  • Rural Poverty head count indices  in 2015/2016 25.6%
  • Urban Poverty head count indices  in 2015/2016 14.8%
  • National income inequality using GINI Coefficient in 2010/11 is 0.298
  • Rural income inequality using GINI Coefficient in 2010/11 is 0.27
  • Urban income inequality using GINI Coefficient in 2010/11 is 0.37
  • National income inequality using GINI Coefficient in 2015/16 is 0.328
  • Rural income inequality using GINI Coefficient in 2015/16 is 0.28
  • Urban income inequality using GINI Coefficient in 2015/16 is 0.38
  • GDP per Capital (in US Dollar) in 1999/00 is 129
  • GDP per Capital (in US Dollar) in 2007/08 is 262
  • GDP per Capital (in US Dollar) in 2015/16 is 794
  • Source:-  Ethiopia's Progress Towards Eradicating Poverty: An  Interim Report on 2015/16
  • Poverty Analysis Study, National Planning Commission, September 2017

 

 

Copyright © Central Statistical Agency - Ethiopia, 2010 / 2018