እንዳለፉት ዓመታት ሁሉ ዘንድሮም የዋናው መኸር ድህረ-ሰብል ምርት ወቅት በጌዚያዊ ና ቋሚ ሰብሎች ማለትም በአገዳ፣ ብርዕ፤ጥራጥሬ ፣ የቅባት እህሎች ፣ በአተክልት ፣ ስራስር እና በቋሚ ሰብሎች እንሰትን ጨምሮ ተሸፍኖ የነበረውን የመሬት ስፋት እና የተመረተው የምርት መጠን ግምት በሰብል ዓይነት መገመት የሚያስችሉ መረጃዎችን ወካይ ከሆኑ ናበ ሳይንሳዊ መንገድ ከመላሀገሪቱ በተመረጡ 2,223 ናሙና የቆጠራ ቦታዎች ውስጥ ኗሪ ከሆኑ ና በናሙ ና ተመርጠው ጥናቱ በተካሄደባቸው 44,362 ቤተሰቦች ውስጥ ከሚገኙ በዘንድሮው የመህር ወቅት ሰብል በማምረት ሥራ ተሰማርተው ከነበሩ ባለይዞታ ገበሬዎች የተሰበሰበ ነው፡፡

ከላይ ቁጥራቸው በተገለጸው ለጥናቱ ተመርጠው በነበሩ የግብርና ቤተሰቦች አባል ከሆኑ ከእያንዳንዱ በዘንድሮው የመኸር ወቅት በሰብል ማምረት ሥራ ከተሰማራ ባለይዞታ ገበሬ በዘንድሮው መህር ሰብል ለማምረት ሥራ ያዋላቸው

1.በሰብል የተሸፈኑ ማሣዎች የመሬት ስፋት መጠን መረጃዎችን፣ እያንዳንዱን በየሰብል ዓይነቱ የተሸፈነ ማሳን በኦሮሚያ ክልል ጂፒኤስ፣  በተቀሩት ክልሎች ደግሞ ሜትርና ኮምፓስ በመጠቀም ተግባራዊ የማሣ ልኬት በማካሄድ ከመስክ በመሰብሰ

2.ጥቅም ላይ የዋለ የግብር ና ምርት ማሳደጊያ ግብዓቶች (ከተፈጥሮ የተገኙ እንደ ፍግ፣ የቅጠላ ቅጠልና ስራ ስር ብስባሽ እና የኬሚካል ውጤት የሆኑ ዩሪያ፣ ዳፕና የመሳሰሉ ማዳበሪያዎች፣ ፀረ-ሰብል ተባይና አረም ማጥፊያ መድሐኒቱች እና ምርጥ ዘር) መጠን መረጃዎችን በተግባር በመመዘንና ለእያንዳንዱ ባለይዞታ በሚደረግ የግል ቃለ መጠይቅ በእያንዳንዱ በሰብል የተሸፈነ ማሣ ላይ ጥቅም ላይ የዋሉ የግብርና ምርት ማሳደጊያ ግብዓቶች መጠን መረጃዎች በግብዓትና በሰብል ዓይነት ከመስክ በመሰብሰ

3.በዘንድሮው መኸር ወቅት በተካሄደው ሰብል የማምረት ሥራ የተገኘውን ጠቅላላ ምርትና የምርታማነት መጠን በሰብል ዓይነት ማስላትና በየሰብል ዓይነቱ የተገኘ ጠቅላላ የምርት መጠንን በዞን፤ በክልልና በሀገር አቀፍ ደረጃ ማቀናበር የሚያስችሉ የምርታማነት መረጃዎችን በሰብል ዓይነት ለጥናቱ ከተመረጡ ከእያንዳንዱቆጠራቦታ በዘንድሮው የመህር ወቅት በአገዳና ብርዕ፤ በጥራጥሬ በቅባት እህሎች ከተሸፈኑ ማሳዎች ለእያንዳንዱ የሰብልዓይነት 10 በሰብል ዓይነቱ የተሸፈኑ ማሣዎቸን በራንዳም/እጣ የተመረጡ ማሳዎችን በመለየት ከእያንዳንዱ የተመረጠ ማሣ   የተገኝውን መረጃ በመመዝገብ፤ ከላይ የተገለጸውን አሰራር ለእያንዳንዱ የሰብል ዓይነት በተመረጡ አስር ማሣዎች በመተግበር የሚገኙ የሰብል ምርታማነት መረጃዎችን ከመስክ በመሰብሰብ ፡

በዋነኛነት ከላይ የተገለጹትንና በርካታ ተዛማጅና ሌሎች መረጃዎችን ከመስክ የመሰብሰብ ሥራ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የመረጃዎችን ጥራትና አስተማማኝነት የማረጋገጥ ሥራ በኤጀንሲው 24 ቅ/ጽ/ቤቶች በሚገኙ የመስክ ሥራ ተቆጣጣሪዎችና ከዋናው መ/ቤት በተውጣጡ ከፍተኛ ባለሙያዎች የመስክ ቁጥጥርና ግምገማ የተካሔደ መሆኑ በጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት ተገልጿል፡፡

 • Inflation rate for the month of May 2018 is 13. 7%
 • National Poverty head count indices  in 2010/2011 29.6%
 • Rural Poverty head count indices  in 2010/2011 30.4%
 • Urban Poverty head count indices  in 2010/2011 25.7%
 • National Poverty head count indices  in 2015/2016 23.5%
 • Rural Poverty head count indices  in 2015/2016 25.6%
 • Urban Poverty head count indices  in 2015/2016 14.8%
 • National income inequality using GINI Coefficient in 2010/11 is 0.298
 • Rural income inequality using GINI Coefficient in 2010/11 is 0.27
 • Urban income inequality using GINI Coefficient in 2010/11 is 0.37
 • National income inequality using GINI Coefficient in 2015/16 is 0.328
 • Rural income inequality using GINI Coefficient in 2015/16 is 0.28
 • Urban income inequality using GINI Coefficient in 2015/16 is 0.38
 • GDP per Capital (in US Dollar) in 1999/00 is 129
 • GDP per Capital (in US Dollar) in 2007/08 is 262
 • GDP per Capital (in US Dollar) in 2015/16 is 794
 • Source:-  Ethiopia's Progress Towards Eradicating Poverty: An  Interim Report on 2015/16
 • Poverty Analysis Study, National Planning Commission, September 2017

 

 

Copyright © Central Statistical Agency - Ethiopia, 2010 / 2018