ሥልጠናው በቆጠራ ቅድመ ዝግጅት ተግባራት አፈጻጸምና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ፣ ከአራተኛው ዙር የሕዝብና ቤት ቆጠራ የትምህርትና ቅስቀሳ መሪ ሰነድ፣ የቆጠራው መጠይቅ፣ ማንዋልና ሜቶዶሎጂ ዝግጅት፣ የቆጠራ ካርታ ዝግጅት፣ የቆጠራ መረጃ ከመስክ ወደ ማዕከል የሚመጣበት ሂደትና ሪፖርት ዝግጅት፣ የአገር አቀፍ የትምህርትና ቅስቀሳ ተግባርና ኃላፊነት እንዲሁም የሚዲያ ተቋማት ሥርጭት በኢትዮጵያ በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮረ ነበር፡፡ የሥልጠናው ተሳታፊዎች በሥልጠናው ማጠቃለያ ላይ ለሕዝብና ቤት ቆጠራ ሥራ ውጤታማ መሆን በሚቀጥለው የሥራ ዕቅዳቸው አስገብተው ሕብረተሰቡን በማስተማርና በመቀስቀስ ለቆጠራው ምቹ ከባቢ ለመፍጠር እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡

በመጨረሻም ስልጠናው ሲጠናቀቅ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ ሚኒስትር ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ለሰልጣኞቹ የሥራ መመሪያ የሰጡ ሲሆን ከሀገር አቀፍ እስከ ክልሎች የሚደራጀው የቆጠራ የትምህርትና ቅስቀሳ መዋቅር እና ሁሉንም ባድርሻ አካላት በማሣተፍና የተቀናጀ የትምህርትና ቅስቀሳ ዘመቻ በመካሄድ ካለፉት ሦስት የሕዝብና ቤት ቆጠራዎች አራተኛው ዙር ቆጠራ በጥራቱና በወቅታዊነቱ የተሻለ እንደሚሆን ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡

የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጄንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢራቱ ይገዙ በበኩላቸው በስልጠናው ማጠናቀቂያ ላይ እንደገለጹት መንግሥት በሕገ መንግሥቱ በተጠቀሰው አኳኋን የሕዝብና ቤት ቆጠራው ወቅቱን ጠብቆ ማከናወን ከሚጠበቅበት ተግባራት ውስጥ ቀዳሚ መሆኑን በመረዳት በየደረጃው ያለው አመራር በቀጣይ ከሚያቅዳቸው ሌሎች የልማት ተግባራት እኩል ጊዜ እንዲሰጡ ግንዛቤያቸውን ከማሳደግ አንጻር የኮሙኒኬሽንና የሚዲያ ተቋማት ድርሻ የጎላ መሆኑን ጠቅሰው ሠልጣኞች ለቆጠራው ስኬት የሚጠበቅባቸውን ታላቅ አገራዊ ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

Contact Us

Ato Biratu Yigezu

General Director

Central Statistical Agency of Ethiopia

Address:- Around Piassa, Back to Taitu Hotel, Adjacent to Ethio Ceramic Head Office

Telephone:-  011-1-11-8777

                        011-1-11-5131

 • Inflation rate for the month of November  2017 is  13.6
 • Total Population size as of July 1, 2017 94,352, 000
 • Total Male Population size as of July 2017 47,365, 000
 • Total Female Population size as of July 2017 46,987,000
 • Total Population size  urban as of July 1, 2017 19,164, 000
 • Total  Male Population size  urban as of July 1, 2017 9,535, 000
 • Total Female Population size  urban as of July 1, 2017 9,630, 000
 • Total Population size  rural as of July 1, 2017 75,188, 000
 • Total Male Population size rural as of July 1, 2017 37,830, 000
 • Total Female Population size rural as of July 1, 2017 37,357, 000
 • Urban Unemployment 2015 17.5%
 • Literacy rate 2009/10 (or recent) 36% of children under weight (too thin for-age) 2011 29.0%
 • GDP per Capital (in US) 2006/07 255.4
 • National Povertyhead count indices and inequality in 2010/2011 29.6%
 • Rural Povertyhead count indices and inequality in 2010/2011 30.4%
 • Urban Povertyhead count indices and inequality in 2010/2011 25.7%

Copyright © Central Statistical Agency - Ethiopia, 2008 / 2016