ከማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ  ህዝብ ግንኙነትና ዳታ ስርጭት ዳይሬክቶሬት 23 May 2016    አዲስ አበባ

የመጀመሪያው አለም አቀፍ የስታቲስቲክስ ጉባኤ በተባበሩት መንግስታት አዳራሽ ተካሄደ፣ የኢትዮጵያ የስታቲስቲክስ ባለሞዎች ማህበር የተመሰረተበትን ሃያአምስተኛ አመትም አከበረ፡፡በምክትል ጠ/ሚኒስትር ማዕረግ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪና የኮሚኒኬሽንና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ ሚኒስቴር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የመክፈቻ ንግግር የተጀመረው ይህ ጉባኤ ለሶስት ቀናት የዘለቀ ሲሆን ከበርካታ የአፍሪካ ሀገራት የስታቲስቲክስ ማህበራትና የአለም አቀፍ ድርጅት ተወካዮች እንዲሁም የማህበሩ አባላት ተሳትፈውበታል፡፡

በመክፈቻ ስነስርዓቱ መግቢያ የኮሚኒኬሽንና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ ሚኒስቴር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል አብዛኞቹ በማደግ ላይ ያሉ ሃገራት  የብሄራዊስታቲስቲክስ ሲስተም መሰናክሎችን በመረዳትና አቅጣጫዎቻቸውን በመፈተሽ ቴክኖሎጅን መረጃዎችን ለመሰብሰብ፣ለማቀነባበርና ለማሰራጨት መጠቀም አሰራራቸውንና መዋቅሮቻቸውን ለመለወጥ የሚያስችል መሰረታዊ አሰራር መሆኑን ተረድተዋል ብለዋል፡፡
 ሚኒስትሩ የሃገራችን የብሄራዊ ስታቲስቲክስ ሲስተምም ሊያከናውን የሚገባውን አቢይስራ እየሰራ እንደሆነ ይታወቃል ያም ሆኖ ወቅታዊነቱን የጠበቀ መረጃ፣ከሎሎች ዳታ አመንጭዎች ጋር በመቀናጀት ረገድ፣ ቴክኖሎጅን በመጠቀምና የማያቋርጥና የተገናዘበ ጥናት በማቅረብ ደረጃ ስራወችን ማሻሻል እንደሚያስፈልጋቸው አሳስበዋል፡፡

በሌላ በኩል ዶ/ር ደብረፅዮን ጉባኤው በሃገራችን በ2010 ለሚካሄደው የህዝብናቤቶች ቆጠራ የውይይት ጊዜ እንደሚኖረውና በዚህም ግባቶችን እንደምናገኝ ጠቁመዋል፡፡

የኢትዮጵያ የስታቲስቲክስ ባለሞዎች ማህበር ሊቀመንበር ዶ/ር ብርሃኑ ተሾመ በበኩላቸው ማህበሩ የተመሰረተበትን 25ኛ አመት ከማክበር ጎን ለጎን በዚህ አለም አቀፍ ጉባኤ ላይ ከፍተኛ የልምድ ልውውጥ አድርገናል ብለዋል፡፡ ከሃያ የአፍሪካ ሃገራት፣ ከተለያዩ አለም አቀፍ ድርጅቶችና ከሃገ ራችን የተለያዩ ከፍተኛ ተቋማትና ኢንስቲትዩሽን የተገኙ በስታቲስቲክስ ሞያ ሰፊ ጥናቶችን ያደረጉና የካበተ ልምድ ያላቸው ባለሞያዎች በጉባኤው ላይ ተሳትፈዋል፡፡ በጉባኤው ላይ ከ40 ያላነሱ ጥናቶች በርካታ ፓናል ውይይቶችና ሰፊ ክርክሮች ተደረገዋል በዚህም አሉ ሊቀ መንበሩ ለምን ሰራቸው ስራዎች ሁሉ የተሻሉ አቅጣጫዎችን ማየትና ማሳየት ተችሏል ብለዋል፡፡በዚህ ጉባኤ ላይ የአፍሪካ ሃገራት የስታቲስቲክስ ማህበራት ስራዎች ተገምግመዋል፣ በማህበሮቻቸውያሉትን መሰናክሎችና መፍተሄወቻቸው ተቃኝተዋል፣ የወደ ፊት አቅጣጫዎች ተነድፈዋል፡፡

ሃገራዊ፣አህጉራዊና አለም አቀፋዊ የልማት እቅዶችን ለማሳካት ትኩረት ለስታቲስቲካል ጥናቶች በሚል መርህ የተጀመረው አለም አቀፍ ጉባኤ ፍላጉትን መሰረት ያደረገ የስታቲስቲክስ ስራ ለውጥ በሃገራችን በቀሩት የአፍሪካና ሃገራትና በቀረው አለም ሁሉ እንዲኖር ማድርግ አስፈላጊነቱ ጎልቶ ታይቷል፡፡ ይህ ጉባኤ ወጣት የስታቲስቲክስ ባለሞያዎች ለመፍጠር፣ለማንቃትና ርዕይ ያላቸው እንዲሆኑ ከማገዙም በላይ ለአፍሪካ የስታቲስቲክስ ማህበረሰብ የጋራ ስራና ቅርርብ መሰረት ይሆናል፡፡

     በሃገራችን በ2010 በሚደረገው የህዝብና ቤቶች ቆጣራን በተመለከተ በተለያዩ ሃገራት ያሉ ልምዶች ተዳሰዋል፣ከባለ ሞያዎች፣ ከህብረተሰቡና ከመንግስት የሚጠበቁ አቢይ ጉዳዮች ታይተዋል፡፡

የማዕከላዊ ስታቲስቲክክስ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢራቱ ይገዙ ስታትስቲክስ የማንኛውም ዘመናዊ አኗኗርና እንቅስቃሴ አካል መሆኑን አስታውሰው የስታስቲክስ የጥናት ውጤቶች የስራ ግልፅነትንና ተጠያቂነትን በዚህም መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ከፍተኛ አስተዋፅዖ ማድርጉን ገልፀዋል፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ ኤጀንሲው በ2010 የሚያከናውነውን የህዝብና ቤቶች ቆጠራን ለማካሄድ ቅድመ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ጠቁመው ቆጠራውንም ሆነ ሌሎች በኤጀንሲው የሚጠኑ ጥናቶች ሁሉ በቴክኖሎጅ ውጤቶች እገዛ እየተከናወኑ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

የኢትዮጵያ የስታቲስቲክስ ባለሞዎች ማህበር የተመሰረተበት 25ኛ አመት አከባበር ማጠቃለያ ላይ ማህበሩ ያለፈውነ አመት ስራ ገምግሞ የቀጣዩን ጊዜ የቦርድ አባላት መርጦ ጉባኤው ማህበሩን በተለያዩ መንገዶች ላገዙት ባለ ሞያዎችና ድርጅቶች ሽልማት አበርክቶ ተጠናቋል፡፡

  • Inflation Rate for the Month of April 2019 is 12.9%
  • National Poverty head count indices  in 2010/2011 29.6%
  • Rural Poverty head count indices  in 2010/2011 30.4%
  • Urban Poverty head count indices  in 2010/2011 25.7%
  • National Poverty head count indices  in 2015/2016 23.5%
  • Rural Poverty head count indices  in 2015/2016 25.6%
  • Urban Poverty head count indices  in 2015/2016 14.8%
  • National income inequality using GINI Coefficient in 2010/11 is 0.298
  • Rural income inequality using GINI Coefficient in 2010/11 is 0.27
  • Urban income inequality using GINI Coefficient in 2010/11 is 0.37
  • National income inequality using GINI Coefficient in 2015/16 is 0.328
  • Rural income inequality using GINI Coefficient in 2015/16 is 0.28
  • Urban income inequality using GINI Coefficient in 2015/16 is 0.38
  • GDP per Capital (in US Dollar) in 1999/00 is 129
  • GDP per Capital (in US Dollar) in 2007/08 is 262
  • GDP per Capital (in US Dollar) in 2015/16 is 794
  • Source:-  Ethiopia's Progress Towards Eradicating Poverty: An  Interim Report on 2015/16
  • Poverty Analysis Study, National Planning Commission, September 2017

 

 

Copyright © Central Statistical Agency - Ethiopia, 2010 / 2018